የእምዩ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ

አካባቢያችንን በማፅዳት ከተማችንን ፅዱ፣ ውብና ለኑሮ ተስማሚ እናደርጋለን ሲሉ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምኒልክ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችም በዛሬው ዕለት አካባቢያቸውን እና በአካባቢው የሚገኙ ተፋሰስና ድልድዮችን አፅድተዋል።

በክፍለ ከተማው የዕየሩሳሌም ቀበሌ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ዘነቡ አዝምቱ እንደተናገረችው በዘመቻ አካቢያቸውን ማፅዳት ከጀመርን አንድ ወር የሆነን ሲሆን የፅዳት ስራውን በዘመቻ በመስራት አካባቢያችን ብሎም ከተማችንን ፅዱ፣ ውብና ለኑሮ ተስማሚ እናደርጋለንም ብላለች።

የምኒልክ ክፍለ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ፅዳትና ውበት ምክትል ኃላፊ አቶ ረቂቅ ሸዋንግዛው በበኩሉ እንደክፍለ ከተማ በሳምንት አንድ ቀን የፅዳት ዘመቻ መጀመራቸውን ጠቁሞ ጊዜው የክረምት ወቅት በመሆኑም አካባቢያቸውን ከማፅዳት ባለፈ የተዘጉ ተፋሶችን ጭምር እያፀዱ መሆኑን ተናግሯል።

ፅዳቱን የሚያከናውነው ማህበረሰቡ በራሱ ፍላጎትና ተነሳሽነት ነው ያሉት ምክትል ኃላፊው አካባቢያቸውን ብሎም ከተማዋን ፅዱ ውብና ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግም አቅደው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የዕምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አሰፈፃሚ አቶ አዲስ ወሰኔ በበኩላቸው ጊዜው የክረምት ወቅት በመሆኑ የክረምት የፅዳት ስራችንን በሳምንት አንድ ቀን እየሰራን ነው ብለዋል።

የፅዳት ስራው የሚተገበረው በክፍለ ከተማው የሚኖሩ የወጣትና የሴት አደረጃጀቶችን በአንድላይ በማስተባበር ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው በየቀበሌው በመንቀሳቀስም ከዋናው አስፓልት ጀምሮ ያሉ ተፋሶችን እና ድልድዮችን ጭምር በማፅዳት ማህበረሰቡን በተፋሰስ መዘጋት ምክንያት ከሚመጣበት የጎርፍ አደጋ እየተከላከልን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም ተግባሩን በቀጣይም አጠናክረን በማስቀጠል ክረምቱ እስኪወጣ ድረስ እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

Our Location

  • Address:
  • Phone: 0913276085
  • Fax:
  • Po. Box:
  • ኢሜይል:

Statistics

0
0
0
0
0