"ሕዝቡ ከልማት ሥራው እንዳይደናቀፍ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በቅንጅትና በትኩረት እየሠራ ነው!!! "ሕዝቡ ከልማት ሥራው እንዳይደናቀፍ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በቅንጅትና በትኩረት እየሠራ ነው ሲሉ የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ምክትል አዛዥና የሰሜን ሸዋ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ብርጋዴል ጄኔራል አበባው ሰይድ ተናግረዋል። መከላከያ ሠራዊቱ ባለፉት ወራት በሰራው ተከታታይ የሕግ ማስከበር ሥራ በዞኑ ስር ባሉ ወረዳዎች የልማት ስራዎች እንዲከናወኑ ማድረጉን ኃላፊው ገልጸዋል። ከየወረዳው የተውጣጡ የፀጥታ አካላት ከበላይ የተሰጠውን አቅጣጫ ተቀብለንና መሬት የመጡ ለውጦችን ለማስቀጠል ኅብረተሰቡን ከፀጥታ ችግር በማላቀቅ የመጡ ለውጦችን ለማስቀጠል እየሠራን እንገኛለን ብለዋል። በተለይም በዚህ መድረክ የፀጥታ ኃይሉ የጎደለውን በመሙላትና በማደራጀት ወደ ሥራ ለማሠማራት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። ጽንፈኛው ኃይል የተሳሳተ መረጃ በሕዝቡ ውስጥ በመንዛት የሠራዊቱን መልካም ስም የማጠልሸት ሥራ ቢሠራም ሕዝቡ በወያኔ ወረራ ጊዜ የነበሩ አመራሮችን ሲያይ ከሠራዊታችን ጎን ተሰልፎ መረጃ በመስጠት እና በሎጂስቲክ ድጋፍ እያደረገልን ይገኛል ብለዋል። በዚህ መድረክም የፀጥታ ኃይሉ የጎደለውን በመሙላትና በማደራጀት ወደ ሥራ ለማሠማራት ያለመ መሆኑን ተናግረዋል። በመድረኩ የኮማንዶና አየር ወለድ ዋና አዛዥና የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል ሹማ አብዴታን ጨምሮ የዞንና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
21
May
2024