23
May
2024
በደብረ ብርሃን ከተማ በጫጫ ክፍለ ከተማ የሜሪሲ ፕሮጀክት የእንስሳት ማዳቀያና ዝርያ ማሻሻያን በየደረጃው የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በጉብኝቱ ላይ የእንሰሳት ባለሙያዎችም ተገኝተዋል። የሜሪሲ ፕሮጀክት 466 የተሻሻሉ የወተት ክልስ ጊደሮችን ለአካባቢው አርሶ አደሮች ማቅረቡን አቶ ቤተ ፍጹም የሜሪሲ ፕሮጀክት ፕሬዘዳንት ተናግረዋል። ወተት ለልጆች ገቢ ለቤተሰብ በሚል ሀሳብ እየሰራ የሚገኝ ፕሮጀክት መሆኑንም አቶ ቤተ ጠቁመዋል። ለህብረተሰቡና ለመንግስት ወደ 5.4 ሚሊዮን የሚጠጋ ብር ድጋፍ ማድረጉን የሜሪሲ ፕሮጀክት ፕሬዘዳንቱ አቶ ቤተ ተናግረዋል። በዚህ ፕሮጀክትም የወተት ላሞችን ዝርያ ማሻሻያ ፕሮጀክት ያለበትን ሁኔታ የደብረ ብርሃን ከተማ እና የሰሜን ሸዋ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎቹ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።