History
Mission of the city administration
|
Vision
|
History of the city with summary የከተማዋ ገጽታ የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ሥር የምትገኝ ክልሉ በመካከለኛ ደረጃ ከፈረጃቸው ከተሞች መካከል አንዷ ነች፡፡ ከተማዋ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ርእሰ ከተማ ከኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ ከአዲስ አበባ 13ዐ ኬ.ሜ ርቀት የምትገኝና ከክልሉ ርእሰ ከተማ ባህር ዳር በ 695 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ Debrebarhan city administration is under the administration of North Showa Zone of the Amhara National Regional Government and is one of the middle-class cities in the region. The city is the administrative capital of North Shewa Zone, which is 13 km away from Ethiopia's capital, Addis Ababa, and 695 km away from Bahr Dar, the capital of the region. የደብረብርሃን ከተማ ታሪካዊ አመጣጥ የደ/ብርሃን ከተማ በአፄ ዘርያእቆብ ዘመነ መንግስት በ1446 ዓ.ም የተቆረቆረች ጥንታዊ ከተማ ነች፡፡ የደብረበርሃን ከተማ ስያሜውን ያገኘችው ከሁለት ቃላት የተወሠዱ ትርጓሜዎች ነው እነሱም ደብረ/አጥቢያ ቦታ/ ማለት ነው፡፡ ብርሃን የሚለው ደግሞ በደስታ ተ/ወልድ የተዘጋጀው የአማራኛ መዝገበ ቃላት እንደሚገልፀው የአጼ ዘርያእቆብ የቅድሰት ስላሴ መቅደስ /ደብር/ የሠሩባት ብርሃን ስለወረደባት በመቅደሱ ስም ደብረብርሃን ተባለ ይላሉ፡፡ ብርሃኑ የታየበት ቀን መጋቢት 1ዐ/1446 ዓ.ም ቀን በቁርባን ጊዜና ሌሊት መዘምራን ሲያገለግሉ ታየ ተብሎ ይነገራል፡፡ ከዚህ በፊት ግን ደብረብረሃን ደብረ ኤባ ትባል እንደነበር በአንዳንድ ፀሐፊዎችና በአፈ ታሪክ ይነገራል፡፡The city of D/Barhan is an ancient city that was founded in 1446 AD during the reign of Emperor Zaryaekob. The city of Debreberhan got its name from the interpretations of two words, which mean "debre/local place". According to the Amharic Dictionary prepared by Joy T/Wold, the meaning of "light" is that it was called "Debre Berhan" after the light that they built on the Temple of the Holy Trinity. It is said that the light appeared on March 1st, 1446 A.D., when he was seen serving in the choir during the Eucharist and at night. But before that, Debrebrehan was called Debre Eba, according to some writers and legends. ምንጭ ፡- ታደሠ አይቸው ከአ/አበባ ዮኒቨርሲቲ የደ/ብርሃን ታሪካዊ እድገት ከተመሠረተበት እስከ 1966 አብዮት ፍንዳታ በአማርኛ ተተርጉሞ የቀረበ፡፡ የከተማዋ የቆዳ ስፋት ደ/ብርሃን ከተማ በ9 የከተማ ቀበሌዎችና በ5 የገጠር ንኡስ ቀበሌዎች የተከፋፈለች ሲሆን የቆዳ ስፋቷም 18081.95 ሄክታር የሚሽፍን የቆዳ ስፋት አላት፡፡ De/Barhan city is divided into 9 urban kebeles and 5 rural sub-kebeles and its surface area is 18081.95 hectares. የከተማዋ መልከዓ ምድራዊ አቀማመጥ ከተማዋ በ90 4ዐ ሰሜን ኬክሮስ /Latitude/ እና በ39ዐ 3ዐ ምስራቅ ኬንትሮስ /longitude/ ላይ ትገኛለች፡፡ ከባህር ወለል በላይ በአማካይ 275ዐ ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ ስትሆን የመሬት አቀማመጧም ሜዳ 86% ወጣ ገባ 1ዐ% ተራራማ 4% ሲሆን የአፈር ዓይነቷም መረሬ፣ ቀይና ቡናማ ነው፡፡
የከተማዋ የአየር ንብረት ሁኔታ የደብረብርሃን ከተማ ሙሉ ለሙሉ የአየር ንብረቷ ደጋማ ሲሆን በአማካይ የሙቀት መጠን 1ዐዐ 39ዐ ሲ.ግ ከፍተኛው እስከ 24ዐ ሲ.ግ ይደርሣል፡፡ የቅዝቃዜ መጠን በ2ዐዐ4 ዓ.ም ታህሣስና ጥር ወር ውስጥ ከዐ በታች -2ዐ ደርሶ እንደነበር ማስታወስ ይቻላል፡፡ አማካይ የዝናብ መጠኗም 946 ሚ.ሜ ነው፡፡ የከተማዋ የህዝብ ብዛት የከተማዋ የሕዝብ ብዛት የበደብረ ብርሃን ከተማ ገንዘብና አካባቢ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የስነ ህዝብ መረጃ እንደሚያመለክተው በከተማ ወንድ 89,579 ሴት 98,934 በድምር 188,513 ህዝብ እንደሚኖር ያስረዳል፡፡
በጋ ከክረምት የሚፈሱ ወንዞች ፡-
በክረምት ብቻ የሚፈሱ ወንዞች ፡-
በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ገባር ወንዞች
በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ኃይቆች ፡-
|