ፈጣን እውነታዎች

ደብረ ብርሃን በሸዋ ክፍለ ሀገር የጅሩ ሸዋ ሜዳ ተጉለትና ቡልጋ አውራጃ ዋና ከተማ ናት። ከተማዋ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ርዕሰ ከተማ ከመሆኗ ባሻገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስም ዋና ጽሕፈት ቤት እዚሁ ይገኛል። በ፲፱፻፺፰ ዓ/ም ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው ደብረ ብርሃን ከተማ የ፷፯ ሺህ ፪፻፵፫ ሰው መኖሪያ ስትሆን ከነሱም ፴፬ ሺህ ፶፭ ወንዶችና ፴፫ ሺህ ፻፹፰ ሴቶች ይገኙባታል ይላል።